የብሥራተ ገብርኤል ኢ/ኦ/ቤ/ክ እድር
የብሥራተ ፡ ገብርኤል ፡ ኢ/ኦ/ቤ/ክ ፡ እድር ፡ መጀመሩን ፡ በእግዚአብሔር ስም ፡ እያበሰርን ፡ የሚከተለውን ፡ መመሪያ ፡ እናስተላልፋለን።
1) የአባላት ፡ ክፍያ ፡ የሚጀምረዉ
October 26/2024-November 30/2024 ባለዉ ፡ ጊዜ ዉስጥ ፡ ብቻ የምንቀበል ፡ መሆኑን እንገልፃለን።
2) የአባላት ፡ ጥቅማ ፡ ጥቅም ማግኘት የሚጀመረው
ከ December 1 ጀምሮ 6 ወር በኋላ (ከ June 1/2025) ጀምሮ ይሆናል ::
ሀ) ለመጀመሪያ ጊዜ የ አባልነት መመዝገቢያ $300
ለ) ፡ ወርሃዊ ፡ ወይም ፡ ዓመታዊ ፡ ክፍያው ፡ በሚከተለው ፡ ስሌት ፡ መሠረት ፡ ይፈጸማል፦
--ግለሰብ ፡ (ያላገባ/ያላገባች) ፡ $20 በወር ($240 በዓመት)
--ባልና ፡ ሚስት ፡ ያለልጅ ፡ $25 ፡ በወር( $300 በዓመት)
--ባልና ፡ ሚስት ፡ ከነልጆቻቸው እድሜያቸዉ 24 እና ከዛ በታች ለሆኑ ልጆች ብቻ)፡ $30 በወር ($360 በአመት)
ሐ) ክፍያው በዚህ አካውንት ገቢ ይሆናል፦
Bisrate Gabriel EOTC Edir
Bank routing: 061000052
Account: 3340 7940 9520
በካሽ: በቼክ እና በዜል መክፈል ይቻላል።
ለዜል ክፍያ 678-598-8411 ን ተጠቀሙ።
መ) ፡ በ ፡ አካል ፡ ለመክፈል ፡ በጽርሃ ፡ ተክለ ፡ ሃይማኖት ፡ የመጀሪያው ፡ ቢሮ ፡ ይምጡ።
የብሥራተ ገብርኤል ኢ/ኦ/ተ/ቤ እድር የመተማመኛ ሰነድ
በአትላንታ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተቋቋመው እድር ባለው የሥራ ጫናና የጊዜ እጥረት ምክንያት የእድሩ መተዳደሪያ ደንብ በጊዜ ሊደርስ ስላልቻለ፣ በጊዜያዊው ኮሚቴ የረቀቀውን የእድሩን መተዳደሪያ ደንብ ተቀብዬ በሰነዱ ለመገዛት በፊርማዬ አረጋግጣለሁ።
መተዳደሪያ ደንቡ በሚጠቅሰው መሠረት ኮሚቴው አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ ከአንድ ዓመት በፊት ይጠራል።
BISRATE GABRIEL EOTC EDIR BINDING AGREEMENT
The bylaw of the Edir established in Debre Bisrate Saint Gabriel Church of Atlatnta has not been completed due to excessive workload and shortage of time. As a result, I agree to accept and be governed y the bylaw as drafted by the adhoc committee by affixing my signature below. The adhoc committee will be calling a general assembly of all the members within one year, as required by the bylaw.