ዘወትር እሁድ፣ ቅዱስ ገብርኤል እለት ወር በገባ በ19ኛው ቀን፣ የአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት እለት ወር በገባ በ24ኛው ቀን እና በዓመት በዓላት ጊዜ ፣ በዓበይት በዓላት፣ በጾመ ፍልሰታ፣ በንግሥ በዓላት እና በሌሎች በዓላት ጊዜየቅዳሴ አገልግሎትና የማኅሌት/የሰዓታት አገልግሎት ያለማቋረጥ ይሰጣል። በቤተክርሰቲያናችን በሳምንት 2 ቀናት ረቡዕ ከምሽቱ 7 pm ጀምሮ እና እሁድ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ይሰጣል። በቤተክርስቲያናችን በየዓመቱ ከ100 በላይ ሕጻናት ክርስትና ይነሳሉ። የሥርዓተ ተክሊል እና ጸሎተ ፍትሐት አገልግሎትም እንዲሁ ይፈጸማል።